FOOD NOTES: Food safety rating system is here!

 January 2017

food safety news

አዲስ የምግብ ደሕንነት ምዘና ስርዓት እዚህ ነው!

ከ ጃንዋሪ፤ 2017 ጀምሮየምግብ ቤቶች የምግብ ደሕንነት ምዘና በምግብ ቤቶች የመስኮት ምልክት ላይ ይታያል፡፡  እነዚህ ምልክቶች ምግብ ቤቶች ምን ያህል የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን እንደሚለማመዱ ደንበኞች እንዲረዱ መረጃ በማቅረብ ያግዛሉ፡፡ 

 ምግብ ቤቶች ባላቸው ዚፕ ኮድ መሰረት በአራት ደረጃዎች  በዚህ አዲስ ስርዓት ውስጥ ይሳተፋሉ፡፡ 

ደረጃ አንድ – ጃንዋሪ፤ 2017
የካርታው ቀይ ቀለም ክፍል 
Seattle - north of I90, Shoreline፣ እና Lake Forest Park area

98101, 98102, 98103, 98104, 98105, 98107, 98109, 98111, 98112, 98113, 98114, 98115, 98117, 98119, 98121, 98122, 98125, 98133, 98139, 98145, 98154, 98155, 98164, 98177, 98195 and 98199.

phase roll in map

ደረጃ ሁለት – ኤፕሪል፤ 2017

የካርታው ወይጠጅ ቀለም ክፍል                                  
ሲያትል – ከ I90 ደቡብ፣ ቫሾን፣ ቤሌቩ፣ መርሰር አይላንድ፣  ኒው ካስል እና ሬንተን አካባቢ 
98004, 98005, 98006, 98007, 98008, 98009, 98015, 98039, 98040, 98055, 98056, 98057, 98058, 98059, 98070, 98106, 98108, 98116, 98118, 98124, 98126, 98134, 98136, 98144, 98146, 98168 and 98178.

 ደረጃ ሶስት – ጁላይ 2017

የካርታው አረንጓዴ ቀለም ክፍል 
ቦዝሄል፣ ውዲንቪል፣ ከርክላንድ፣ ሬድመንድ፣ ኢሳኳ፣ ስካይኮሚሽ፣ ካርናሽን፣ ዱቫል እና Kent አካባቢ

98010, 98011, 98014, 98019, 98022, 98024, 98025, 98027, 98028, 98029, 98030, 98031, 98032, 98033, 98034, 98035, 98038, 98041, 98042, 98045, 98050, 98051, 98052, 98053, 98064, 98065, 98072, 98073, 98074, 98075, 98077, 98083, 98089, 98224, 98288.

ደረጃ አራት – ኦክቶበር 2017

የካርታው ሰማያዊ ቀለም አካባቢ 
ኦበርን፣ በሪን፣ ፌደራል ዌይ፣ ኖርማንዲ ፓርክ እና ቱክዊላ አካባቢ

98001, 98002, 98003, 98023, 98047, 98063, 98092, 98093, 98138, 98148, 98158, 98166, 98188, 98198, 98354, 98422.

ምግብ ቤቶች በ 2017 ውስጥ በተለመደው ሁኔታ ሲመረመሩ፤ የመስኮት ምልክቶቻቸውን ይቀበላሉ፡፡ 

 ማወቅ ያለብዎች ነገር፡፡

  • ማየት የምንፈልጋቸው የምርመራው ሂደት እና የምግብ ደሕንነት ልምምዶች እንደነበሩ ይቀጥላሉ፡፡   አዲስ የተቀየረው ነገር፤ በእያዳንዳንዱ የምርመራ ሂደት መጨረሻ ላይ፤ ንግድዎ አንዱን የምግብ ደሕንነት ምዘናዎቻችንን ይቀበላል፡፡ ስለ አራቱ የምዘና ክፍፍሎች የበለጠ መረጃ ለማግኘት፤ ከታች ይመልከቱ፡፡  
  • የምዘናዎ ውጤት፤ በምርመራዎ ዝርዝር ሪፖርት ላይ እና በምግብ ቤትዎ በሚለጠፈው ምልክት ላይ ይሆናል፡፡ 
  •  የመስኮት ምልክቶቹ፤ ጠቅላላው ሕዝብ ለማየት በሚቀልለው ስፍራ ላይ ይለጠፋል፡፡ ይህ ማለት፤ ምልክቶቹ በምግብ ቤቶቹ መስኮት ላይ ወይም ከምግብ ቤቱ ዋና መግቢያ አምስት ጫማ ክልል ውስጥ ይለጠፋሉ ማለት ነው፡፡   የእያንዳንዱ ምግብ ቤት ክፍት ስፍራ የተለያየ ነው፤ ስለዚህ እርስዎ እና የእርስዎ መርማሪ ምልክቱን መለጠፊያ ጥሩ አመቺ ስፍራ ለማግኘት አብራችሁ መስራት ትችላላችሁ፡፡ 
  • የምግ ደሕንት ምዘና ከእያንዳንዱ የምርመራ ዙር ሂደት በኋላ ይሻሻላል፡፡  በኪንግ ካውንቲ ውስጥ ያሉ ምግብ ቤቶች በአማካይ በዓመት ውስጥ ከ 1-3 ጊዜ ይመረመራሉ፡፡ የምግብ ምዘና ውጤትዎን፤ በየዓመቱ ጥሩ የምግብ ደሕንነት በመለማመድ ማሻሻል ይችላሉ፡፡ ጥሩ የምግብ ደሕንነት ስለመለማመድ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከታች ይመልከቱ፡፡
  • ስጋት 1፣ 2 እና 3 የምግብ ምስረታዎች አሁን በአዲሱ የምዘና ስርዓት ውስጥ ተካትተዋል፡፡ 
  •  እያንዳንዱ ስለ ምዘናዎቻቸው ይግባኝ የመጠየቅ መብት አሏቸው፡፡ የምርመራ ዝርዝር ሪፖርት በተሰጥዎት በ 10 የስራ ቀናት ውስጥ፤ ስለ ምርመራው የይግባኝ ጥያቄ ማስገባት  ይችላሉ፡፡  
  •  የምግብ ፕሮግራም ተቋም፤ አዲሱ የምዘና ስርዓት ለአካቢያችን በአግባቡ እንደሚሰራ ለማየት ይገመግመዋል፡፡ እንደ ግምገማው አካል፤ አንዳንድ ምግብ ቤቶች የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን እንዲመለከቱ የምልከታ ምርመራ ይቀበላሉ፡፡ መርማሪው መጀመሪያ ላይ ይህንን አይነት ምርመራ እየተቀበሉ ከሆነ ያሳውቅዎታል፡፡ እነዚህ ምርመራዎች በምግብ ደሕንነት ምዘና ውጤትዎ ላይ ወይም የምግብ ቤቱ የምርመራ ታሪክ ላይ ምንም አይነት ተፅዕኖ አይኖራቸውም፡፡  

 ስለ አዲሱ የምግብ ደሕንነት ምዘና ስርዓት የበለጠ መረጃ እዚህ አለ

የምግብ ደሕንነት ምዘና ክፍፍሎች 


Food Safety Rating Categories

ማሻሻል አለበት

ባለፈው ዓመት ውስጥ ምግብ ቤቱ በሕዝብ ጤንነት- ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ ተዘግቶ ነበር ወይም ምግብ ቤቱ የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን ለማስተካከል ተደጋጋሚ የመልሶ ምርመራ ማድረግ ይኖርበታል፡፡  

ደሕና

ምግብ ቤቱ፡ ባለፉት አራት ምርመራዎች ብዙ ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ነበሩት፡፡

ጥሩ

ምግብ ቤቱ፡ ባለፉት አራት ምርመራዎች አንዳንድ ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ነበሩት፡፡

እጅግ በጣም ጥሩ

ምግብ ቤቱ፡ ባለፉት አራት ምርመራዎች ምንም ወይም ጥቂት ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ነበሩት፡፡


ከምግብ ቤቶች ምዘና በስተጀርባ ያለው ምንድን ነው?

የምግብ ቤቶች የምዘና ክፍፍል የሚወሰነው በሶስት ዋና ዋና አካላት ነው:

  • በጊዜያት ውስጥ ያሉ የምግብ ደሕንነት ልምምዶች ሂደት፡፡ ጥሩ የምግብ ደሕንነት በየዕለቱ መተግበር አለበት፡፡ የምግብ ደሕነት ምዘና የመስኮት ምልክቶች ምግብ ቤቶች በአንድ ነጠላ ምርመራ ብቻ ሳይሆን፤ በረዥም ጊዜያት ውስጥ ምን ያሕል እየተንቀሳቀሱ እንዳለ ያሳያል፡፡ የምግብ ቤቶች የምግብ ደሕንነት ምዘና የሚወሰነው ከምግብ ቤቱ ያለፉት አራት ተከታታይ ምርመራዎች የቀይ አደገኛ ጥሰት ነጥቦች ነው፡፡
  • የብቃት ደረጃ፡፡ የኪንግ ካውንቲ ነዋሪዎች፤ ምግብ ቤቶች ምርመራውን ማለፋቸውን ወይም መውደቃቸውን ባለፈ ማወቅ ይፈልጋሉ፡፡ የምግብ ቤት መስኮት ምልክቶች፤ ምግብ ቤቶች ዝቅተኛውን የመስፈርት ደረጃ ከማሟላት ባለፈ ምን ያህል የምግብ ደሕንነት ልምምዶችን እንደሚለማመዱ ያሳያል፡፡
  • በስፍራ ያለ ምዘና ፡፡ ደንበኞች ባሉበት ዚፕ ኮድ ወይም አካባቢ የመመገብ አዝማሚያ አላቸው፡፡   በስፍራ ያለ ምዘና፤ ምግብ ቤቶች በአቅራቢያቸው ካሉ ምግብ ቤቶች ጋር ሲነፃፀሩ ምን ያህል የምግብ ደሕንነት ላይ እንደሚሰሩ ለደንበኞች ትክክለኛ እና ጠቃሚ መረጃ ያቀርባሉ፡፡  በተጨማሪም፤ በአንድ አካባቢ ያሉ ምግብ ቤቶች ተመሳሳይ የምግብ መርማሪ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ መርማሪዎቻችን ጥልቅ በሆነ ስልጠና ውስጥ ያለፉ እና ሁሉም ትኩረታቸው በምግብ ደሕነነት ላይ ነው፡፤  በስልጠናውም እንኳ፤ በጥቂቱ  ለየት ያለ የምርመራ ስልቶች ሊኖራቸው ይችላል፡፡   የስፍራ ምዘና፤ በምርመራ የምዘና ስልቶች የሚፈጠሩ ልዩነቶችን ለማካካስ ይረዳል፡፡ የእያንዳንዱ ምግብ ቤቶች አማካይ ውጤት በተመሳሳይ ዚፕ ኮድ ወይም አካባቢ ካሉ ከሌሎች ምግብ ቤቶች ጋር ይነፃፀራል፡፡ በስፍራ ያለ ምዘና የሚተገበረው ለከፍተኛ 3 ክፍፍሎች ነው፡፡ በእያንዳንዱ ክፍፍል ስር የሚመደቡ የምግብ ቤቶች አቅራቢያዊ የፐርሰንቴጅ ዝርዝር እንደሚከተለው ነው:
Approximate percentages of restaurants in categories

ቀይ አደገኛ ጥሰት ምንድን ነው?

ቀይ አደገኛ ጥሰቶች ማለት የምግብ አያያዝ ልምምዶች ሲሆኑ፤ እንደሚገባው ካልተተገበሩ፤ በእርግጠኝነት ወደ ምግብ ወለድ በሽታዎች ያመራሉ፡፡ 

Red critical violations

ለምግብ ቤትዎ የምግብ ደሕንነት ስልጠና ከፈለጉ፤ ከሕዝብ ጤንነት – ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ በየዓመቱ አንድ የትምህርት ምርመራ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ተጨማሪ የመማሪያ ምርመራ ለመጠየቅ ከፈለጉ: ዶ/ር ዳማሪስ ኢስፒኖዛ በ Damarys.espinoza@kingcounty.gov, ቢሮ: 206-263-8583 ወይም በሞባይል: 206-940-9545.

ስለ አዲሱ የምግብ ደሕነት ምዘና ስርዓት በፅሑፋችን ላይ የበለጠ ያንብቡ Yሕዝብ ጤና የውስጥ አዋቂ፡፡ ፡፡

የመገናኛ ብዙሃን ፍላጎት

አዲሱ የምዘና ስርዓት ከሚሰጠው ትኩረት እና ፍላጎት የተነሳ ምግብ ቤትዎ ስለ አዲሱ የምግብ ደሕነት ምዘና ስርዓት እና የምግብ መስኮት ምክቶች ለመጠየቅ በመገናኛ ብዙሃ ሊገኙ ይችላሉ፡፡  ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ማውራትም ሆነ አለማውራት የእርስዎ ምርጫ ነው፡፡ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ማውራት ካልፈለጉ፤ ይህንን የመገኛ አድራሻ መረጃ በመስጠት በቀጥታ ከእኛ ጋር እንዲነጋገሩ መንገር ይችላሉ: 

የሕዝብ ጤንነት – ሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ የግንኙነት ቡድን

ካርሊ ቶምሰን

carley.thompson@kingcounty.gov ወይም 206 477-3058

 የመገናኛ ብዙሃን ፍላጎት የእርስዎ ዚፕ ኮድ በአዲሱ ስርዓት ውስጥ ሲካተት ተፅዕኖ ሊያሳድርብዎት ይችላል፡፡

በዚህ ፤ ከምግብ ቤት ባለቤቶች እና ከመላው ሕዝብ ጋር ስለ አዲሱ የምግብ ደሕንነት ምዘና ስርዓት ማስታወቂያ ለመስጠት የማሕበረሰብ ስብሰባዎች ይኖረናል፡፡ ዝርዝር ማብራሪያዎች በቅርብ ይሰጣሉ፡፡

ስለ አዲሱ የምግብ ደሕንነት ምዘና ስርዓት ወይም ስለ መጪው የማሕበረሰብ ስብሰባዎች ለማግኘት ጥያቄ ካልዎት: ዶ/ር ዳማሪስ ኢስፒኖዛ በ Damarys.espinoza@kingcounty.gov , ቢሮ: 206-263-8583 ወይም በሞባይል: 206-940-9545.