የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ የ 2027 የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠንን አስታወቀ

Office of Labor Standards logo - press release version

Press Release

For Immediate Release

Contact Information
Cynthia Santana
Phone: 206-256-5219
Email: cynthia.santana@seattle.gov

የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ የ 2027 የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ መጠንን አስታወቀ

Seattle, WA – (ሴፕቴምበር 28፣ 2026) –የስራ መደብ መስፈርቶች ቢሮ (OLS፣ Seattle Office of Labor Standards) ከጃንዋሪ 1፣ 2027 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የሲያትል የመነሻ ደመዎዝ መጠን ላይ ጭማሪ መደረጉን አስታወቀ። ዓመታዊ የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪ በ Minimum Wage Ordinance (ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን) መሰረት የተደረገ ነው። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዙ የሰራተኛውን የስደተኝነት ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ ተፈጻሚ ይሆናል። የዝቅተኛ መነሻ ደመወዝ ጭማሪ በሲያትል ታኮማ ቤልቪው አካባቢ በሸማቾች ዋጋ መረጃ ጠቋሚ (CPI-W) ላይ ተመስርቶ ያለውን የዋጋ ግሽበት መጠን የሚያንጸባርቅ ይሆናል።

ከጃንዋሪ 1፣ 2027 ጀምሮ፣ ሁሉም ትላልቅ እና አነስተኛ ንግዶች ለሰራተኞች በሰዓት $22.14 ይከፍላሉ።

ዝቅተኛ መነሻ የደመወዝ መጠን በከተማው ገደብ ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ዝቅተኛውን ደመወዝ ያስቀምጣል። የሲያትል ወቅታዊ የ2026 ዝቅተኛ ደመወዝ በሰዓት $21.30 ነው።

OLS የ 2027 የስራ ደረጃዎችን የተመለከቱ መረጃዎችን የያዘ የተሻሻለ የስራ ቦታ ፖስተር ለሁሉም በ Seattle የንግድ ፈቃድ ለሚሰሩ አካላት ይልካል። የስራ ቦታው ፖስተር ቅጂ በእንግሊዘኛ እና በ 30 ሌሎች ቋንቋዎች ተተርጉሞ በቅርቡ የሚገኝ ይሆናል። በ Seattle የሰራተኛ ደረጃዎች ላይ የቅርብ ጊዜ ዝማኔዎችን ለማግኘት ለ OLS ጋዜጣ በ OLS ድረገፅ ላይ ይመዝገቡ።  

  • እርዳታ ለአሰሪዎች፦ የ Seattle የመነሻ ደመዎዝ እና ሌሎች የስራ ደረጃዎችን በማክበር ረገድ ነጻና ግላዊ እገዛ ለማግኘት፣ ወደ 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ laborstandards@seattle.gov ወይም እዚህ ጠቅ አድርገው ኦንላይን የመጠየቂያ ቅጽ ይሙሉ።
  • እርዳታ ለሰራተኞችና ለሕዝቡ፦ ጥያቄ ለመጠየቅ፣ ቅሬታ ለማቅረብ ወይም መረጃ ለመስጠት፣ በስልክ ቁጥር 206-256-5297 ይደውሉ፣ በ laborstandards@seattle.gov ኢሜይል ይላኩ፣ ወይም የድረገጽ ቅጽ ለመሙላት እዚህ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

###